ታላቁ ተስፋ - Great Hope - Official

ታላቁ ተስፋ - Great Hope - Official

@-greathope-official · 5.5K subscribers · 489 videos · English

ታላቁ ተስፋ ከተስፋዎችሁሉ በላይ የሰው ሁሉ ሃሳብ እና አይን በቅርቡ በሚገለጠው በታላቁ ተስፋ በክርስቶስ ላይ ይሆን ዘንድ የሚያሳስብ የወንጌል አገልግሎት ነው። በዚህ አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ በደስታ እንቀበላለን። እንዲሁም ሼር በማ…

Episodes

11:35

የጥበብ መንገድ_ መልእክት ለወጣቶች_ 106 Message to young people

25 views · 15h ago · 11:35

ብዙ ጊዜ ወጣቶች እንደ እርሾ በመሆን አእምሮን የሚቀይር ነገር ያስፈልገናል ይላሉ። የሚያስፈልገው ነገር የክርስቲያን ተስፋ ነው። ሐይማኖት ለአማኝ አፅናኝና ወደ እውነተኛ የደስታ ምንጭ የሚመራ እርግጠኛ መሪ ነው። ወጣቶች በተመስጦና በጸሎት የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት አለባቸው። ይህንን ሲያደርጉ ትርፍ ጊዜያቸውን ከዚህ ለተሻለ ነገር መዋል እንደማይችል ያውቃሉ። «የጥበብ መንገዶች ምቹ መንገዶች ናቸው፣ መንገዶችዋም በሙሉ ሰላም ናቸው።» ጳውሎስ ለቲቶስ በጻፈው መልእክቱ ወጣቶች ራሳቸውን የሚገዙ እንዲሆኑ ይመክራል። “እንዲሁም ወጣቶች ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው። የሚቃወም ሰው ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር ሲያጣ እንዲያፍር፣ በነገር ሁሉ መልካምን በማድረግህ ምሳሌ የሚሆን ራስህን አሳይ፤ በትምህርትህም ደኅንነትን፣ ጭምትነትን፣ጤናማና የማይነቀፍ…

10:56

መዝናኛና መደሰቻ_ መልእክት ለወጣቶች 105

80 views · 3d ago · 10:56

እግዚአብሔር አእምሮኣችንን ለመሳብና ፍላጎት እንዲኖረን ለማድረግ ዙሪያችንን በተፈጥሮ ውብ ነገሮች ከቧል። የተፈጥሮ ግርማዎችን ከእርሱ ባህሪይ ጋር እንድናዛምድ እቅዱ ነው። የተፈጥሮ መጽሐፍን በታማኝነት ብናጠና ኖሮ ስለ ዘላለማዊው ፍቅሩና ኃይሉ ለማሰላሰል ፍሬያማ ምንጭ እናገኝ ነበር። በጨርቅ ላይ የሚያማምሩ ቅቦችን የሚሰራውን የሰዓሊን ሥራ ብዙዎች ያደንቃሉ። የብዙዎች ያላቸው ኃይል በሙሉ ለስዕል ሥራ የ#ዋለ ቢሆንም ስራዎቻቸው ግን ከተፈጥሮው እጅግ በጣም የራቁ ናቸው፡፡ ሥነ ሥዕል በተፈጥሮ ውስጥ የሚታየውን ፍፅምና በፍፁም ሊደርስ አይችልም። ብዙ ክርስቲያኖች የምሽቱን የፀሐይ ጥልቀት የሚገልፅ ሥዕል ሲያዩ እጅግ ይደሰታሉ። የሰዓሊውን ችሎታ ያመልካሉ። ነገር ግን በግርማ የተሞላውን እውነተኛውን ፀሐይ ደመና በሌለባቸው ምሽቶች ሁሉ የማየትን እድል…

28:55

ታላቁ ተጋድሎ_ ምዕራፍ 38 _ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ

118 views · 1w ago · 28:55

ይህ ትረካ በአሜሪካዊቷ ጸሃፊ ኤለን ጂ ኋይት በእግዚአብሔር መሪነት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ሲሆን የመጨረሻውን ማስጠንቀቂያ በተመለከተ ለመጨረሻው ዘመን ክርስቲያኖች የተሰጠውን ይህንን ማስጠንቀቂያ ከታላቁ ተጋድሎ 38ኛ መዕራፍ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ መልካም የበረከት ጊዜ ይሁንላችሁ፡፡ ለምትሰጡት አስተያየት ሁሉ ጌታ ይባርካችሁ፡፡ Telegram

9:54

የእናት ሽልማት _ መልእክት ለወጣቶች _ 98 MESSAGE TO YOUNG PEOPLE

78 views · 3w ago · 9:54

በዚህ ክፍል የቤተሰብን ስብእና ግንባታ ፣ የልጆችን ታዛዥነት ዋጋ እና እግዚአብሔርን የመፍራትና የመታዘዝ አስፈላጊነት እንቃኛለን፡፡ ወጣቶች ሊኖራቸው ስለሚገባው አስተዳደግ በዚያ ውስጥ ያለውን የእናት ከባድ ሃላፊነትም እንመለከታለን፡፡ ተባረኩ፡፡ Telegram

4:57

ቁጠባና ልግስና_ 96 መልእክት ለወጣቶ _MESSAGE TO YOUNG PEOPLE

112 views · 3w ago · 4:57

በዚህ ክፍል ቁጠባ እና ልግስናን በተመለከተ እና ቁጠባን በመለማመድ የጌታን ስራ ማፋጠን እንደሚግባን እናያለን፡፡ መልካም የበረከት ጊዜ ይሁንልዎ፡፡ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ያበረታቱን ፣ ላይክም ያድርጉልን፡፡ ተባረኩ፡፡ ክርስቶስ ብቀርብ ይመጣል፡፡ አሜን Telegram

52:35

ታላቁ ተጋድሎ_ ምዕራፍ 39_ የመከራ ዘመን

360 views · 3w ago · 52:35

ምዕራፉ በመካከለኛው ዘመን ክርስቲያኖች ላይ ይደርስ ስለነበረው መከራ ፣ በመጨረሻው ዘመን በክርስቲያኖች ላይ ስለሚደርሰው ስደትና የያእቆብ መከራ ጋር ምን እንደሚያገናኘውና ሰይጣን በሰማይ የጀመረው አመፅ በምን ሁኔታ እንደሚደመደም የሚያብራራ ክፍል ነው። መልካም የበረከት ጊዜ ይሁንላችሁ። በጥልቀት በመስማት ለምትሰጡኝ አስተያየት ከልብ አመሰግባለሁ ተባረኩ።

6:54

ራስን የማስደሰት ክፋቶች_ መልእክት ለወጣቶች 94 _Message to young people

195 views · 1mo ago · 6:54

ሰዎች ጥቃቅን በሚመስሉ ወጪዎች ይጠመዳሉ፡፡ እነዚያ ጥቃቅን ወጪዎች ግን ቢጠራቀሙ ብዙ ድሆችን የመርዳት አቅም አላቸው፡፡ በማያስፈልጉን ጌጣጌጦች አምላካችን የሰጠንን ገንዘብ አናባክነው፡፡ ተባረኩ Telegram

Showing the 15 most recent episodes. Everything plays right here on Pod Atlas.

Have thoughts about ታላቁ ተስፋ - Great Hope - Official? Share them with other listeners.

Discuss this podcast

More Society, Culture & Lifestyle podcasts

← Back to all podcasts